መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) ጋር የገባበትን ጦርነት ሳይዘገይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም መያዝ እንዳለበት ኦፌኮ አሳሰበ

የፌደራሉ መንግስት ለትግራይ ክልል የሰላም እጁን እንደዘረጋው ሁሉ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ሳይዘገይ ይያዝ ሲል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረንስ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማሳረጊያ ባወጣው የአቋም መግለጫው አሳስቧዋል፡፡

በቅርቡ የፌደራሉ መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ጦርነትን ለማቆም ያሳለፉትን ውሳኔ በበጎ እንደሚመለከተው ተናግሮ ፤ በፍጥነት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ እንዲቀይሩት ጠይቋል፡፡
ይሆን እንጂ ላለፉት ሶስት አመት በላይ ኦሮሚያን እያመሳት ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት የሚገባውን ትኩረት ተነፍጎታል ብሏል፡፡

በመሆኑም የፌደራሉ መንግስት የሰላም እንጁን ለትግራይ ክልል እንደዘረጋው ሁሉ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ሳይዘገይ እንዲይዝም ጠይቋል፡፡

ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ እና ገለልተኛ እንዲሁም ተአማኒነት በሌላቸው አካላት የሚመራ ብሔራዊ ምክክር የሃገሪቱን ችግር ይፈታል ብለን አናምንም ሲልም ገልጻል፡፡
ይህ እንዲሁም በሁሉም የሀገረቱ አካባቢዎች የተኩስ አቁም ስምምነት ይድረስ ፤ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በጦርነቱ ከተሳተፉ ሀይሉች ጋርም ድርድር እንዲጀመር በማድረግ ግጭቱች ይቁሙ፣ ያሉትን የህግ ማነቆዎችን በማንሳት ብሔራዊ ምክክር ላ እንዲሳተፉ ይደረግ ብሏል፡፡

የብሔራዊ ምክክር አዋጁ ሊዘጋጅ የሚገባውም በጋራ ስምምነት ሆኑ ኮሚሽነሮችም ምክክሩ ላይ በሚሳተፉ አካላት ሊመረጡ ይገባል ነው ያለው፡፡
በተለያዩ ግጭቱች ከቀያቸው ለተፈናቁሉ ዜጎችም አስቸኳ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ከአለም አቀፍ ረጂ ተቋማት ጋር እንደሰራም ጠይቋል፡፡
መጋቢት 19፣ ቀን 2014 ዓ.ም
ያይኔአበባ ሻምበል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *