ዘመን ባንክ በድረገፅ የሚደረጉ ክፍያዎችን ከማስተር ካርድ የክፍያ ዘዴዎች ጋር በማጣመር በዘመን ባንክ ፣ ማስተር ካርድ እና ቪዛ ካርድ ግብይት በዲጅታል መንገድ ክፍያ የሚያከናኑበት የክፍያ አማራጮችን ማቅረቡን አስታውቋል፡፡
የባንኩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አምሃ ታደሰ እንዳሉት ደንበኞች ባሉበት ሆነው ክፍያ ሊፈጽሙ የሚችሉበት አሰራር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሆቴሎች፣ የንግድ ሱቆች፣ የጉዞና አስጎብኚ ድርጅቶች፣የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እና ሌሎችም የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።
አገልግሎቱ የአየር መንገድ ደንበኞች የ ኢ-ኮሜርስ አሰራርን በመጠቀም ቦታ እንዲይዙ እና የበረራ ቲኬቶችን በበይነ መረብ አማካኝነት እንዲከፍሉ ያደርጋቸዋል ብለዋል ።
ከባንኩ ደንበኞች ውጭ ያለ የትኛውም ማህበረሰብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል አቶ አምሃ ተናግረዋል።
ዘመን ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር በ 2013 ከንክኪ ነፃ የተጓዦች ካርድ ማስተዋወቁ የሚታወስ ነው።
መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
እስከዳር ግርማ











