በርካታ ተሸከርካሪዎች በአዳማ እና በመተሀራ ከተሞች ቆመው እንዳሉና በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ኤትዮ ኤፍ ኤም ከአከባቢው ነዋሪዎች ሰምቷል፡፡
ነዋሪዎቹ እንደነገሩን በአከባቢው የጸጥታ ችግር መኖሩን ተናግረው ሰዎችም መገደላቸውን ነግረውናል ፣ በዚህ የተነሳ ከድሬዳዋ አዲስ አበባ ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ የባቡር አገልግሉት መቋጡን ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
ኤትዮ ኤፍም ጉዳዩን በተመለከተ ወደ ኢትዮ -ጅቡቲ ባቡር ድርጅት ደውለን ጉዳየጡ የሚመለከታቸውን ሃላፊ ዶ/ር አብዲ ዘነበን አናግሯል፡፡
ዶ/ር አብዲ ‘‘የተፈጠረውን ችግር እያጣራን ነው ፡፡ችግሮን እንዳጣራንም ለደንበኞቻችን እናሳውቃለን” ብለውናል፡፡
ችግሩ ከጽጥታ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ለጠየቅናቸው ጥያቄ ዶ/ር አብዲ ‘‘እንዲህ አይነት ችግሮች ካሉ የጸጥታ አካላት ያሳውቃሉ ፣እኛ የሰርቪስ አገልግሎት ነው የምንሰጠው ፣ ከዚህ ጋር የተገናኙ ችግሮች ካሉ ግን እናሳውቃለን” ብለዋል፡፡
‘‘ችግሩ ብዙ የሚያሰጋ አይደለም” ያሉት ዶ/ር አብዲ አገልግሉቱን በአፋጣኝ ለማስጀመር ግን ጥረት ላይ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡
መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም
ያይኔአበባ ሻምበል