“ የምታገለው ለመላው ጭቁን ህዝብ ነው” የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በሃገሪቱ ላሉ ፖለቲካዊ ችግሮች መንስኤ መደረጉ ትክክል እንዳልሆነ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ነግረውናል፡፡

እንደ እነዚህ ያሉ ሁኔታችን ለማስገንዘብ እና መፍትሔዎችን ለህዝቡ ለማመላከት በሄደበት እና በደረሰበት ሁሉ እንቅፋቶች አላንቀሳቅስ አንዳሉት ጨምረው ተናግረዋል፡፡
አቶ ለሚ እንዳሉት ፓርቲያቸው የሚታገለው ለመላው ጭቁን ህዝብ ነው፣ ሁሉን ጥለን ወደ ሀገር ቤት የገባነው የትግል ስልታችንን ቀይረን በሀገሪቱ ህግ እና ደንብ ለመተዳደር ነው ብለውናል፡፡

‹‹ ኦነግ ሸኔ የሚባል በሌለበት መንግስት በፖርላማ ጭምር እንዳለ ተናግሯል፣ እኛ እስከምናውቀው ድረስ ግን በዚህ ስያሜ የሚጠራ ሃይልየለም ›› ካሉ በኃላ አያይዘው ‹‹ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ የድርጅቱ አንድ ክንፍ እንደነበረውና ፣ ከለውጡ ጋር ተያይዞ የድርጅቱ አመራር ወደ ሀገር ከገባ ወዲህ ራሱን ችሎ እየተቀሳቀሰ ያለ ነው፣ እኔ እሱን የምመለከተው በዚህ መንገድ ነው ›› ብለውናል፡፡

ኦነግ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚከሰቱ ጥቃች ስለሚገደሉት ንጹሀን ዜጎች ያዝናል ያሉት አቶ ለሚ ‹‹ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የችግር መንስኤ ሳይሆን ፤የችግር መፍትሔ እንደሆነ ሚዲያውም ሆነ የኢትዮጲያ ህዝብ እና መንግስት ማወቅ አለበት›› ብለዋል ፡፡

የትጥቅ ትግልን ሳይሆን ሰላማዊ የትግል መንገድን መርጠናል የምንታገል የፖለቲካ ማህበር ነን ሲሉ አክለው ነግረውናል፡፡” የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር መንስኤ ሳይሆን የመፍትሔ አካል መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ መንግስትም ሆነ ሚዲያው ሊያውቀው ይገባል ብለውናል፡፡

መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

ያይኔአበባ ሻምበል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *