በሚዛን አማን ከተማ ከ11ሺህ በላይ ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸው ተነገረ፡፡

ሚዛን አማን ከተማ ባሉ የጤና ተቋማት ለ 15 ሺህ 4መቶ 72 ሰዎች ላይ በተደረገ የወባ በሽታ ምርመራ በ11 ሺህ 4መቶ 68 ሰዎች ላይ በሽታው መገኘቱ የገለጹ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል ተብሏል፡፡

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግርማዬ ቤርሙስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፣ በከተማዋ የወባ ወረርሽኝ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱ በአንድ ቤት በአማካኝ ሁለትና ሶስት ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን በተደረገው የቤት ለቤት ክትትል ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

በጤና ተቋማት በቀን እስከ 100 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ማረጋገጥ የተቻለ መሆኑን ሀላፊው ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡
ከህክምና ጋር ተያይዞም ሁሉም የጤና ተቋማት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት በዞኑ መኖሩን ነው አቶ ግርማዬ ቤርሙስ የተናገሩት፡፡

በ2012 ዓ.ም የተሰራጨው አጎበር ለ5 ዓመት የሚያገለግል በመሆኑ ተጨማሪ አጎበር ማቅረብ እንዳልተቻለ ሀላፊው ጠቅሰዋል፡፡
በሽታው ከሚዛን አማን በተጨማሪም በሌሎችም አካባቢዎች እየተሰራጨ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *