በጉራጌ ዞን በአራት ወረዳዎች በእሳት አደጋ 80 ያህል ቤቶች መቃጠላቸው ተነግሯል፡፡
አደጋዎቹ የደረሱት በእዣ ወረዳ ፣ በቀቤና ፣በቸሀ እና በአበሽጌ ወረዳ እንደሆነ የዞኑ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካዛል ሀዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
የተቃጠሉ ቤቶች በቁጥር በእዣ ወራዳ 26 ቤቶች፣በቀቤና 42 ቤቶች፣ በቸሀ 5 ቤቶች እንዲሁም በአበሽጌ ደግሞ 7 ቤቶች መቃጠላቸውን አቶ ካዛል ነግረዉናል፡፡
በዞኑ በደረሱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና የአደጋዎቹ መንስኤ እንዲሁም የደረሰው የንብረት ውድመት ገና በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም











