በኢትዮጵያ የባንክ ብድር ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ 250 ሺ አይበልጥም መባሉን ሰምተናል

አብዛኛው ህዝብ ከባንክ ቤቶች ብድርን ማግኘት የሚችልበት፤ በቂ ተቀማጭ ገንዘብ በቁጠባ ደብተሩ አለመኖሩ በኢትዮጵያ የባንክ ብድር ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ 250 ሺ እንዳይበልጥ ማድረጉን ሰምተናል፡፡

አሁን ላይ 17 ሚሊዮን የባንክ ሂሳብ ከከፈቱ ሰዎች መካከል 6 በመቶ የሞባይል ባንኪንግ ስርዓት ተጠቃሚ ሲሆኑ ፤ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች ደግሞ 1 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል ።

83 በመቶ የሚሆኑ የአካውንት ባለቤቶች ደግሞ እስካሁን ድረስ የባንክ ደብተርን በመጠቀም ገንዘብን ወጪና ገቢ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡
ይህም ማህበረሰባችን ከእጅ ንከኪ ነጻ የሆነ የገንዘብ ዝውውርን መፈጸም ሆነ የኤሌክተሮኒክስ ንግድን በመጠቀም ግብይትን የማድረግ ልምዱ ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል ተብሏል፡፡

እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ ሰዎች ባሉበት ሆነው ማንኛውንም አይነት አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ ሲስተም መዘርጋቱን አሪፍ ፔይ የተሰኘ ኩባንያ ገልጿል።

አሪፍፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አ.ማ በ3.1 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን ለአነስተኛ እና ጥቃቅን የንግድ አይነቶች ከባንክ ብድር ማግኘት የሚያስችላቸውን ስርአት ማመቻቸቱን አስታውቋል ።

አሩፍ ፔይ እስካሁን ከ8 ባንኮች ጋር በጋራ እየሰሩ ሲሆን ከ2 ተጨማሪ ባንኮች ጋር ደግሞ በቅርቡ ስራ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል ።

በኢትዮጵያ የባንክ ብድር ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ 250 ሺ አካባቢ በመሆኑን በዘመናዊ የፋይናንስ ስርአት ውስጥ ያልተካተቱ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ክፍሎችን ድርጅቱ ባዘጋጀው የወረቀት የመከታተያ ቅጽ አማካኝነት ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

በሚያዝ ንብረት አልያም በፋይናንስ ዝውውር ሪፖርት ምክንያት ባንኮች ብድር የሚነፍጓቸውን አነስተኛ እና ጥቃቅን ንግዶች በአሪፍፔይ መተግበሪያ አማካኝነት የሚፈጽሙት ግብይት እና የገንዘብ ዝውውር ተመዝግቦ በቀላሉ ከመተግበሪያው የሚያገኙትን የፋይናንስ ሪፖርት በማቅረብ የባንክ ብድር ማግኘት እንደሚችሉ አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል ።

አገልግሎቱንም በይፋ ከጀመረበት ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ 800 መቶ ሺ ብር የሚሆን ዝውውር አሪፍ ፔይ ስርዓትን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፉንም መከወኑ የአሪፍ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አክስዮን ማህበር መስራች አቶ ሃብታሙ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ይህንንም ቁጥር በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ውስጥ ወደ 1 ቢሊየን ብር ከፍ ለማድረግ መታቀዱንም ነግረውናል።

የአሪፍ ፔይ ገንዘብ ማስተላለፊያ በይፋ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ በስፍራው የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንደ አሪፍ ፔይ ያሉ የኦንላይን ክፍያ ስርዓቶች የኤሌክትሮኒክስ ንግድን ለማሳለጥ ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።

ሚያዝያ 07 ቀን 2014 ዓ.ም
መሳይ ገ/መድህን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *