“ከደቡብ ሱዳን አልፈው የሚመጡ አርብቶ አደሮች ዝርፊያ እና የህጻናት ስርቆት እየፈጸሙ ነው “ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል

በምዕራብ ኦሞ ዞን በሱርማ እና በሞርሌ አቅጣጫዎች ከደቡብ ሱዳን አልፈው የሚመጡ አርብቶ አደሮች ዝርፊያ እና የህጻናት ስርቆት እየፈጸሙ መሆናቸው በአከባቢው ላይ ስጋት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቡች ክልል የሰላም እና የጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

እኚህ ድንበር ተሻጋሪ አርብቶ አደሮች ለዝርፊያ ሲሉ በሚፈጽሙት ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን እንዲሁም ንብረት መውደሙን አቶ አንድነት ገልጻዋል፡፡
ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ወቅታዊ ሆኔታ አንጻር ክልሉ ባለው ሀይል ከአርብቶ አደሮች ጋር በመቀናጀት ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን አንስተው ችግሩ ግን ከፍተኛ በመሆኑ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተነጋገርን ነው ይላሉ፡፡

ከመከላከያ እና ከሌሉች የፌደራል ተቋማት ጋር ተቀናጅተን በቀጣይ ስራዎችን አጠናክረን ለመስራት ዝግጅት እያደረገግን ነው የሚሉት ሀላፊው ፣በእኛ አቅም የሚሰሩትን ለመፈጸም ጥረታችንን ቀጥለናል ብለዋል ፡፡

አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቀድሞ በደቡብ ክልል ውስጥ ካሉት 26 ዞኖችን ይዞ በቅርቡ የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል ፡፡

ያያኔአበባ ሻምበል

ሚያዝያ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *