የዊክሊክስ መስራች የሆነዉ ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

አዉስትራሊያዊዉ ኤዲተር፣ ጸሀፊ እና አክቲቪስት ጁሊያን አሳንጅ እ.ኤ.አ በ2010 በአሜሪካ የጦር ሃይሎች መረጃ ተንታኝ ቼልሲማኒንግ አማካኝነት ባገኘዉ እና ባሰራጨዉ ሾልኮ የወጣ መረጃ ምክንያት አለምአቀፋዊ ትኩረትን አግኝቶ ነበር፡፡

የለንደን ፍርድ ቤት አሳንጅ ለአሜሪካ መንግስት ተላልፎ ይሰጥ የሚለዉን የርክክብ ትዕዛዝ ለእንግሊዝ መንግስት ከላከ በኋላ ፣ እዛዉ አሜሪካ ዉስጥ በስለላ ህግ እንደሚዳኝ ተገልጿል፡፡

በ 2010 ዊክሊክስ ባሳተመዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ምስጢራዊ ፋይሎች እና ዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ አሳንጅ በአሜሪካ መንግስት በ18 የወንጀል ክሶች የሚፈለግ ሲሆን፣ በዚህ ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 175 አመታት የሚደርስ የእስር ፍርድ እንደሚጠብቀዉም አልጄዚራ ዘግቧል

ሚያዝያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

እስከዳር ግርማ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *