አለማችን ለጦር መሳርያ ግዢ 2 ትሪሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች፡፡

በፈረንጆቹ 2021 ላይ ለጦር መሳርያ ግዢ ከሁለት ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ መደረጉን ቲንክ ታንክ አስነብቧል፡፡

የአለማችን 62 ከመቶ የመሳሪያ ግዢ የፈጸሙት አምስት ሀገራት እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም መሰረት አሜሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ እንግሊዝ እና ሩስያ በተከታታይ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ግዢ የፈጸሙ ሀገራት ተብለዋል፡፡

እስካንዲቪያዊቷ ሀገር ስዊድን ለተከታታይ ሰባት አመታት ከፍተኛ የጦር መሳርያ ግዢ የፈጸመች ሀገር ተብላለች፡፡

በስቶኮልም የሚገኝው አለም አቀፍ የሰላም ጥናት ማእከል እነዚህ ሀገራት አምና ፈጽመውት ከነበረው የመሳርያ ግዢ በበለጠ ዘንድሮ በ0.7ከመቶ ጭማሪ አሳይተዋል ሲል አትቷል፡፡

ሩስያ ዩክሬንን ከወረረችበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ በ2.7ከመቶ የመሳርያ ግዢ ፍላጎቷ መጨመሩ ነው የተነገረው፡፡

ባጠቃላይ እስካሁን ድረስ 65.9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንዳደረገች ነው ቲንክ ታንክ ያስነበበው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *