ዳሽን ባንክ ደንበኞች ማንኛውንም እቃ በዱቤ ለመሸመት የሚችሉበትን “ዱቤ ፔይ” የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ፡፡

ባንኩ ሰዎች የሚፈልጉትን እቃ ለመግዛት ብር ቢያጥራቸው እንኳን፤በዱቤ መግዛት የሚችሉበትን አገልግሎት በዛሬዉ እለት በይፋ ማስጀመሩን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ “ዱቤ ፔይ” የሚባል ሲሆን፤ የነጋዴውን ምርት ለሸማቾች በዱቤ መልክ የሚያቀርብ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ይህም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ፤ ሰዎች የሚፈልጉትን ነግር ከመግዛት እንዳያግዳቸው እና በቀላሉ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡

የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ደንበኞች የዳሽን ባንክ የዱቤ የሂሳብ ደብተር በማውጣት እና የዱቤ ፔይ መተግበሪያን በማውረድ መመዝገብ እንደሚችሉ፤የባንኩ ዲጂታል ባንኪንግ ዋና ኦፊሰር አቶ ዮሃንስ ሚሊዮን ተናግረዋል፡፡

ታዲያ በማንኛው ሰዓት መግዛት የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ያለምንም ችግር በዱቤ መልክ መግዛት እንደሚችሉ ኦፊሰሩ ተናግረው፤ እንደ ገንዘቦቹ ልክ የአንድ ዓመት፤የ6 ወር እና የ3 ወር ዱቤን የመመለሻ ሲስተሞች መዘርጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዳሽን ባንክ እና የመተግበሪያው አበልጻጊ ድርጅት ኤግልላይን በዛሬው እላት ይህን ሲስተም ማስኬድ የሚቻልበትን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የዱቤ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ደንበኞች ከሚያወጡት የዱቤ የሂሳብ ደብተር እና ከሚያወርዱት መተግበሪያ በተጨማሪ ከሚሰሩበት ቦታ ደሞዛቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት፤ካልሆነም ንብረት ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡
መተግበሪያው በሃገራችን 4 ቋንዎች ማለትም በአማርኛ፣ትግረኛ፣አፋን ኦሮሞ እና ሶማሊኛ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ አማራጭ መቅረቡ ተነግሯል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *