የአለም ፕሬስ ቀን በመላው አለም እየተከበረ ይገኛል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ ባህል እና ትምህርት ተቋም ዩኔስኮ በየአመቱ የሚከበረው የፕረስ ቀን በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል፡፡

የአለም ፕሬስ ቀን የሚከበርበት ዋነኛ ምክንያት ሁሉም መንግስታት፣ የሚድያ ደህንነትን እንዲያረጋግጡ ያለመ ቢሆንም፣ ጋዜጠኞች ስራቸውን ካለምንም ፍርሃት፣ ጥቃት፣ ዛቻና ፍትህ የጎደለው እስራት ለመስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው፡፡

የድንበር አልባ ጋዜጠኞች ቡድን፣ በዚህ አመት የአለም ነጻ ፕሬስን አስመልክቶ ባወጣው አሃዝ፣ ኢራን ከ 180 ሃገሮች 174ኛ ሆናለች።

እንደ ቻይና፣ ሰሜን ኮርያ፣ ኤርትራ፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረብያ እና ሌሎችም ሀገራት አሁንም ድረስ የጋዜጠኞች መብት ያልተከበረባቸው ሀገራት ናቸው ሲል ተቋሙ ባወጣው መረጃ አትቷል፡፡
በተለይም በኢራን የጋዜጠኞች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል አስነብቧል፡፡

የሚድያ ነጻነት ድርጅት፣ መንግስት ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር ስለሚያደርጋቸው፣ ጭካኔ የተመላባቸው ጥረቶች ጠቅሷል።
ምርመራዎችን፣ እስራቶችንና ግድያዎችን እንደሚያካትቱ ድርጅቱ ጠቁሟል።
የጋዜጠኞች ህይወት አደጋ ላይ የሚወድቅባቸው ሃገሮች ኢራን ብቻ አይደለችም ይላል።

ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ኮሚቴ፣ ባለፈው አመት በስራቸው ምክንያት የተገደሉት ጋዜጠኞች ቁጥር ከእጥፍ በላይ ሆኗል ሲልም ያክላል።
በርካታ ጋዜጠኞች የተገደሉባቸው ሀገሮች፣ ሜክሲኮና አፍጋኒስታን መሆናቸዉንም አብራርቷል፡፡

/CPJ/ በሚል የእንግሊዘኛ አህጽሮት የሚታወቀው የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ኮሚቴ፣ አምና በስራቸው ምክንያት የታሰሩት ጋዜጠኞች ብዛት፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስገንዝቧል።
ባለፈው አመት ከታሰሩት ጋዜጠኞች አብዛኞቹ፣ ቻይና ቱርክና ግብጽ ውስጥ መሆናቸውን CPJ ገልጿል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *