የሶማሊያ ምርጫ ግንቦት 15 እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረዉ የሶማሊያ ምርጫ ግንቦት 15 በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለታል፡፡

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዉን እያስተባበረ የሚገኘዉ የፓርላማዉ ኮሚቴ እንደገለጸዉ፣ ከላይኛዉ ምክርቤት ወይም ከሴኔቱ 54 እንዲሁም ከታችኛዉ ምክርቤት ደግሞ 275 በአጠቃላይ 329 ህግ አዉጭዎች 10ኛዉን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ይመርጣሉ ብሏል፡፡

እጩዎቹ ተመራጮች በግንቦት 11 እና 12 በፓርላማዉ ተገኝተዉ ከምርጫዉ በፊት ስለ ፖሊሲያቸዉ ገለጻ እንደሚያደርጉ ኮሚቴዉ አክሎ ገልጿል፡፡

ከታቀደለት የጊዜ ገደብ በ15 ወራት የዘገየዉ የ2022 የሶማሊያ ምርጫ በባህሪዉም ሆነ በዉጤቱ በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ባሉ ሀገራት መካከል ያለዉ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት ላይ እንደ ማዕበል ከፍ ያለ ከባድ ተጽዕኖ ያሳድራል ተብሏል፡፡

የምርጫዉ ዕለት እ.ኤ.አ በግንቦት 15፣ 1943 በ13 ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች ነጻ እና የተባበረች ሶማሊያን ለመፍጠር ታስቦ የተመሰረተዉ የሶማሊያ ወጣቶች ሊግ 79ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ታሪካዊ ቀን ላይ እንደሚዉልም ተነግሯል፡፡

@ሲጂቲኤን አፍሪካ

በእስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.