የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሀንስ አያሌው እንዳሉት ባለፈው አመት ከነበረው 40 በመቶ የተበላሸ ብድር አሁን ወደ 28 በመቶ ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ይህን 3.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለው በተለያየ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩትን ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ባንኩ ካለው የተበላሸ ብድር በአንድ አመት ውስጥ ከ14 በመቶ በታች፣ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማድረስ መታቀዱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።
በረድኤት ገበየሁ
ግንቦት 01 ቀን 2014 ዓ.ም











