በስምንት አመታት ወስጥ አንድ ሚሊዮን ዜጎች በካንሰር በሽታ ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ሲል አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

በአፍሪካ ሀገራት ከኤች አይ ቪ ኤድስ በላይ የካንሰር በሽታ ስር እየሰደደ መምጣቱን ጥናቱ አመላክቷል፡፡
የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ባስጠናው ጥናት መሰረት፣ በአሁኑ ሰአት በአፍሪካ በካንሰር በሽታ ከሚያዙ 100 ሰዎች መካከል 80 ከመቶ የሚሆኑት ህይወታቸው ያጣሉ፡፡

ለበሽታው ፈዋሽ መድሃኒት ካለመኖሩ ጋር ተዳምሮ በስምንት አመት ወስጥ እስከ አንድ ሚሊዮን ያህል ዜጎች በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡

ከካንሰር አይነቶች መካከል በሴቶች ላይ የሚከሰተው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከፍተኛውን ቁጥር ይወስዳል የሚል ግምቱን አስቀምጧል፡፡
በአህጉሪቱ በአመት እስከ 500ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በዚሁ በካንሰር በሽታ ለህልፈተ ህይወት እንደሚዳረጉም ነው ጥናቱ ያመላከተዉ፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ለበሽታው የሰጡት ትኩረት አነስተኛ እንደሆነ የጠቆመው ጥናቱ፣ በአንዳንድ ሀገራት የካንሰር ህክምና እንኳን በቂ እንዳልሆነም ጠቁሟል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *