‹‹ ኢትዮጵያ በሜዳዋ ውድድር የማድረግ ፈቃድ አላገኘችም›› – የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን [ካፍ] ለፌዴሬሽናችን በላከው ደብዳቤ ኢትዮጵያ በሜዳዋ የምታደርገው
መጪውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በሜዳዋ የማከናወን ፍቃድ እንዳላገኘች የ7 ገፅ ሪፖርት አባሪ በማድረግ
አስታውቋል።

በጥቅምት ወር ኢትዮጵያ ጨዋታ የምታደርግባቸው ስታዲየሞች የካፍ መመዘኛዎችን ያሟሉ ባለመሆናቸው ውድድሮች እንዳይደረግባቸው እገዳ እንደጣለ የሚታወስ ሲሆን ከዚያ ወዲህ በተለይም የባህር ዳር ስታዲየም ደረጃን ለማሻሻል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

በዚህም በርካታ የማሻሻያ ስራዎች ከተሰሩ በኋላ ካፍ ስታዲየሙን እንዲገመግም የኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ባለሙያ በማስላክ ባሳለፍነው ሐሙስ ምልከታ ተከናውኗል።

ዩጋንዳዊው የካፍ ባለሙያ ባቀረቡት ሪፖርት መነሻነት ካፍ ባለ ሰባት ገፅ ሪፖርት ለኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን የላከ ሲሆን የካፍን መመዘኛዎች ማሟላት ባለመቻሉ በዚህ ወር የሚያደርገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ በሌላ ሀገር ሜዳ እንዲያከናውን እና እስከ ግንቦት 4 ድረስም የሚጫወትበትን ስታዲየም እንዲያሳውቅ አያይዞ አስታውቋል።

በሪፖርቱ ላይ የስታዲየሙ ደረጃ በካፍ መመዘኛ ተቀባይነት እንዲኖረው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሶ መስራት እንደሚገባ በመግለፅ በ10 የተለያዩ መመዘኛዎች ላይ ድምዳሜዎችን አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በሜዳዋ ውድድር የማድረግ ፍቃድ ሳታገኝ ቀርታለች

የመጫወቻ ሜዳ እና በዙርያው የሚገኙ አካባቢዎችን በተመለከተ
– የመጫወቻ ሜዳው በአዲስ የተፈጥሮ ሳር እንዲተካ ፣ አውቆማቲክ የውሃ ማጠጫ እንዲኖረው ጠቁሞ በዘርፉበሚሰራ ኩባንያ አማካኝነት የመግጠም እና እንክብካቤ ስራ እንዲራ ጥቆማ አድርጓል።
– በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ ጠባብ ጎሎች በስታዲየሙ ውስጥ እንዲኖሩ
– የተጠባባቂ እና የጨዋታ አመራሮች መቀመጫ የኢንተርናሽናሽናል ስታንዳርድ ባለማኧላቱ እንዲቀየር፣
ከአሰልጣኞች መቆምያ ቢያንስ አምስት ሜትር የራቀ እና በአግባቡ የተሸፈነ የተጠባባቂ እና የጨዋታ አመራር መቀመጫ እንዲሰራ
– የካፍ መመዘኛን የሚያሟላ የስታዲየም ፓውዛ መኖር ይኖርበታል
– ተለዋጭ የኃይል አቅርቦት መዘጋጀት ይኖርበታል።
መልበሻ ክፍልን በተመለከተ
– የመልበሻ ክፍሎች ያሉባቸው ደረጃ የካፍ መመዘኛን ባለሟሟላታቸው ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መልክ መሰራት
ይኖርባቸዋል።
– በመልበሻ ክፍል የሚገኙት ምንጣፎች ሙሉ ለሙሉ ተነስተው በማያንሸራትት ወለል መተካት ይኖርባቸዋል።
– የመታጠብያ ፣ የመፀደጃ ቤት መቀመጫ ፣ ሎከሮች ፣ የማሳጅ ጠረጴዛ ፣ ታክቲክ ቦርድ ፣ሙቅ እና ቀዝቃዛ ውሃ ፣ አየር ማቀዝቀዣ እና የመሳሰሉትን ከሟሟላት በተጨማሪ የጥራት ደረጃቸው ከፍተኛ መሆን ይኖርባቸዋል።
– በመልበሻ ክፍል የሚገኝ የማሟሟቂያ ስፍራ በሰው ሰራሽ ሳር መሸፈን ይኖርበታል።
– ካፍ የሚጠቀምባቸው ቢሮዎች መታደስ ይኖርባቸዋል።
– ለኳስ አቀባዮች እና ባንዲራ የሚይዙ ታዳጊዎች ክፍል መሟላት ይኖርበታል የሜዲካል ክፍልን በተመለከተ
– በካፍ መመዘኛ መሠረት የሜዲካል ቁሳቁሶች መሟላት ይኖርባቸዋል።
– አውቶማቲክ ቬንትሌተር፣ የቀላል ቀዶ ጥገና ቁሳቁሶች፣ ኦክስጂን፣ እና የመሳሰሉ ከ23 በላይ መሳርያዎችን
እንዲያሟላ ይጠበቅበታል።
– የዶፒንግ መቆጣጠርያ ክፍል ከመልበሻ ክፍል አቅራቢያ መሆን ይኖርበታል
– የዶፒንግ መቆጣጠርያ ክፍሉ ላልተፈቀደላቸው አካላት ዝግ መሆን ይሆነርበታል
– መፀዳጃ ቤቱ ከዶፒንግ መቆጣጠርያ ክፍል አጠገብ መኖር ይኖርበታል።
ተመልካች ተኮር ጉዳዮችን በተመለከተ
– ሙሉ የስታዲየም ክፍሎች ክፍሎች መታደስ ይኖርባቸዋል። ንፅህና እና የቀለም ቅብ እንዲሁም ለአንድ ሰው
አንድ ደረጃውን የጠበቀ መቀመጫ ወንበሮችን ያካተተ መሆን ይገባዋል።
– መቀመጫዎችን የሚሸፍን ጣርያ ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል
– የምግብ እና መዝናኛ አገልግሎት በሁሉም የስታዲየም ክፍል ሊኖር ይገባል
– ስታዲየሙ የደህንነት አና የእሳት አደጋ ሰርቲፍኬት ከሚመለከተው አካል ማግኘት ይኖርበታል።
– አስፈላጊ ጠቋሚ ምልክቶች በስታዲየሙ ሊኖሩ ይገባል
– የኤሌክትሪክ ሲስተም መሟላት ይገባዋል
– የፓርኪንግ ቦታ በአግባቡ የተለየ እና ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ ቦታ መዘጋጀት ይኖርበታል
– ስታዲየሙን ሙሉ የሚያሳይ መቆጣጠርያ ሊኖረው ይገባል። አሁን የሚገኘው መቆጣጠርያው ያልተገባ ቦታ ላይ
በመደረጉ በተገቢው ቦታ ላይ መሆን ይኖርበታል።
– ግዙፍ ስክሪን መተከል ይኖርበታል
– የድንገተኛ መብራት ሲስተም ያስፈልጋል
– ለተመልካች የመጀመርያ ህክምና መስጫ አቅርቦት መኖር ይገባል
– ለአካል ጉዳተኞች አመቺ መሆን ይገባል
የቪአይፒ እና ቪቪአይፒ በተመለከተ
– መቀመጫዎች ዘመናዊ እና ከፍተኛ ምቾት ያላቸው እንዲሆኑ፣ ቋሚ እና የማይነቀል መቀመጫ መተከል
ይኖርበታል
– ለቪቪአይፒ እና ቪአይፒ እንግዶች አገልግሎት የሚሰጥ ከፍ ያለ ደረጃውን የጠበቀ ላውንጅ መሰራት
ይኖርበታል።
– የተሟላ እና ደረጃውን የጠበቀ ፓርኪንግ
– የቪአይፒ ቦታው የተሸፈነ ባለመሆኑ ለዝናብ እና ለመሳሰሉት ተጋላጭ እንዳይሆን ጣርያ ሊገጠምለት
ያስፈልጋል።
– የመስታውት መለያ በቪአይፒ ፣ ቪቪአይፒ እና በሚዲያ ሩም መካከል ያስፈልጋል።
ሚዲያን በተመለከተ
– የሚዲያ ትሪቡን በተሟሉ ቁሳቁሶች መደራጀት ይኖርበታል
– የፕሬስ ኮንፈረንስ ክፍል እስከ 50 ዘናዊ መቀመጫዎችን ፣ እና የድምፅ እና ተዛማጅ ሲስተሞች የተሟሉለት
መሆን ይገባቸዋል።
– የቴሌቪዥን እና ብሮድካስት ፣ የጨዋታ አስተላላፊዎች ቦክስ መሻሻል ይኖርበታል።
የልምምድ ፋሲሊቲን በተመለከተ
– የልምምድ ቦታው መብራት፣ ቢያንስ አንድ ሙሉ ቡድን የሚያስተናግድ የመልበሻ ክፍል ያለው ፣ የመታጠቢያ
እና መፀዳጃ ቤት የተሟላለት ፣ አምቡላንስ አቅርቦት ያለው፣ አስማማኝ ደህንነት ያለው መውጫ እና መግቢያ ያለው
መሆን ይኖርበታል።

ካፍ ከሪፖርቱ ጋር አያይዞ የሆቴል እና ሆስፒታል አቅርቦቱ በቂ መሆኑን ገልፆ የካፍ መመዘኛዎችን ሊያሟላ
በሚችል መልኩ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ እድሳት መደረግ እንዳለበት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የባህር ዳር ስታዲየም ፈቃድ ባያገኝም ኢትዮጵያ ውድድሯን በሜዳዋ
እንድታከናውን የባህር ዳር ስታዲየምን ሁኔታ ለማሻሻል ላደረገው ከፍተኛ ጥረት የአማራ ክልል መንግስትን
እያመሰገነ በቀጣይ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎቿን በሀገሯ እንድትጫወት የሚያስችላትን ፈቃድ እስክታገኝ ድረስ ፌዴሬሽንችን ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥል ለመግለፅ ይወዳል።


ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *