የሩሲያ እና ዩክሬን ግጭትን ተከትሎ ሩሲያ ላይ ተደራራቢ ማዕቀቦች በመጣላቸው ምክንያት፣ የኒውክሌር ጣቢያው ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ተብሏል።
ግዙፍ አቅም እንዳለው የተነገረለት ይህው የኒውክሌር ማባሊያው፣ በ2023 ማምረት ይጀምራል የሚል እቅድ ተይዞለት እንደነበር ተነግሯል።
ለፕሮጀክቱ መዘግየት ዋነኛው ምክንያት በገንዘብ እና በመሳሪያዎች ላይ ሊደረጉ በሚችሉ እንዲሁም እየተደረጉ ባሉ እገዳዎች የተነሳ ነው ተብሏል።
በአጠቃላይ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተዉ ፕሮጀክቱ፣ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ውስጥ እንደማይጠናቀቅ ከወዲሁ እየተገመተ ይገኛል።
የቱርክ የኒውክሌር ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዳስታወቀው ፣የፕሮጀክቱ የፋይናንስ ወጪ ሙሉ በሙሉ የሚሸፈነው በሩሲያ መንግስት አማካይነት መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በረድኤት ገበየሁ
ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም











