‹‹ሩሲያ ወደ ሌሎች ሀገራት የምትልካቸዉ የምግብ ግብዓቶች የዓለምአቀፉን የምግብ ቀዉስ ይፈታሉ›› የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፡፡

ከሩሲያ፣ዩክሬን እንዲሁም ከቤላሩስ የሚላኩ እንደ ምግብ እና ማዳበሪያ ያሉ ግብዓቶች ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የከፋ እና የማያቆም የምግብ ቀዉስ መመልከት የማይፈልግ ከሆነ በዓለምዓቀፉ ገበያ ላይ እንዲሸጥ ሊፈቅድ ይገባዋል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ተናግረዋል፡፡

እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ለምግብ ቀዉሱ ከዩክሬን የሚላኩ የምግብ ግብዓቶች እንዲሁም ከሩሲያ እና ቤላሩስ የሚላኩ የምግብ እና የማዳበሪያ ግብዓቶች በገበያዉ ላይ ከመፈቀዳቸዉ ዉጭ ሌላ አስተማማኝ የሆነ መፍትሄ የለም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላለዉ የምግብ ቀዉስ ምክንያት ከመሆን በተጨማሪ የሩሲያ ወታደራዊ ጥቃት፣ የአየር ንብረት ለዉጥ እና ኮሮና የምግብ ቀዉሱን እየጎዱ የነበሩ ጉዳዮችን የበለጠ እንዲባባሱ አድርጓቸዋል ብለዋል ዋና ጸሀፊዉ፡፡

ሩሲያ ፣ ዩክሬን እንዲሁም ቤላሩስ የምግብ እና ማዳበሪያ ግብዓቶች ዋና አምራቾች መሆናቸዉን የተናገሩት ዋና ጸሃፊዉ፣ ይህን አለመቀበል አንችልም ሲሉ መናገራቸዉን አር ቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *