“ኢትዮ ፎረም” የተሰኘው የዩ ቲዮብ መገናኛ ብዙኃን አዘጋጅ የሆነው ያየሰው ሽመልስ ዛሬ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ የካ አባዶ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን ጠበቃው አቶ ታደለ ገብረመድሀን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የሲቪል ልብስ ለብሰው ነበር የተባሉ አራት የጸጥታ ኃይሎች፤ ጋዜጠኛው ያየሰውን ወደ የካ አባዶ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ለትንሽ ጊዜ እንዳቆዩት የዓይን እማኞችን ጠቅሰው ጠበቃው አስረድተዋል።

የጸጥታ ኃይሎቹ ከቆይታ በኋላ ጋዜጠኛውን ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት መሄዳቸውንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
ዘግቧል።

ያየሰው ምንም እንኳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተወስዷል ቢባልም፤ ጠበቃውም ሆነ ቤተሰቦቹ እስካሁን ድረስ በአካል እንዳላገኙት ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ፡- ኢትዮጵያን ኢንሳይደር

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.