ከሰሞኑ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ያስተላለፉትን ዛቻ ተከትሎ ቻይናም ጠንከር ያለ ምላሽ እየሰጠች ትገኛለች፡፡

ባይደን ቻይና የተሳሳተ ውሳኔ በታይዋን ላይ እርምጃ ቢያስወስዳት፣ የምንሰስተው የጦር መሳሪያ አይኖረንም ሲሉ ዝተዋል፡፡

ባይደን በቀጠናዉ ሲያደርጉት የነበረዉን ጉብኝት አጠናቀዉ ከመውጣታቸው ቻይና በአይነቱ ልዩ እና በርካታ ወታደሮች የተሳተፉበት ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ እያካሄደች ትገኛለች፡፡

የሃገሪቱ የጦር ሃይል ይህንን ያረጋገጠ ሲሆን ራስገዟ ታይዋን የኔ አካል ናት የምትለው ቻይና፣ ውህደቱን በአጭር ጊዜ ያለምንም ደምመፋሰስ እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳለው የቻይና መንግስት በተደጋጋሚ ሲያሳውቅ ቆይቷል፡፡

ይህ ወታደራዊ ልምምድ በአየር እና በባህር ላይ የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ፍጥነት ወደ ልምምድ የተገባው ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ምላሽ ለመስጠት መሆኑ ተነግሯል፡፡

አሜሪካ፣ ሩስያ ዩክሬንን የወረረች እንደሆን የማትወጣዉ ችግር ዉስጥ ትገባለች ስትል ዛቻዎችን ስታሰማ ነበር፡፡
ዩክሬን ተወራ በርካታ ከተሞቿ ወድመው እና ሚሊየኖች ለስደት ተዳርገዉ እያለ አሜሪካ ከሩስያ ጋር ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከመግባት እንደተቆጠበች ነው፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *