የሳምንታዊው የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን ወንድሙ ለዶቼቬለ ተናገረ።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ የጋዜጠኛው የሥራ ባልደረቦች ” በሁለት መኪና የመጡ ሲቪል የለበሱና የፀጥታ ኃይሎች ነን ያሉ ሰዎች ይዘውት ሄደዋል” ሲሉ በስልክ ነግረውኛል ብሏል።

የወሰዱት ሰዎች ማን እንደሆኑና የት እንደወሰዱት እንደማያውቅም ታሪኩ ደሳለኝ ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአመት በፊት ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከመጽሔት ሥራው ጋር በተገናኘ ለአንድ ቀን ታስሮ መለቀቁ ይታወሳል።

ጋዜጠኛው በኢሕአዴግ ዘመን በሚሰራቸው የሕትመት የጋዜጠኝነት ሥራዎቹ ምክንያት ለሦስት ዓመትት ታስሮ እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.