በአዲስ አበባ ብቻ በየዓመቱ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ በሽታ እንደሚያዙ ተነገረ፡፡

ሪች ኢትዮጲያ በ ‘USAID Urban TB LON Project’ አማካኝነት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸዉ፣ በአዲስ አበባ በየዓመቱ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ በሽታ ይያዛሉ፡፡

በመዲናዋ የቲቢ በሽታ መድሀኒት ከሚወስዱ ዜጎች መካከልም 40 በመቶ የሚያህሉት መድሀኒቱን በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚያቋርጡ ነው የተነገረው፡፡
ታማሚዎቹ መድሀኒቱን የሚያቋርጡበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ የምግብ እጥረት ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በቀን 400 የሚደርሱ ሰዎች በቲቢ በሽታ ሲያዙ 52 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡

በአለም የቲቢ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁ 30 አገራት መካከል ኢትዮጲያ አንዷ መሆኗም ተገልጿል።

በዚህም ሳቢያ በአንድ አመት ውስጥ ከ21 ሺህ በላይ የሚሆኑ የቲቢ ህሙማን ህይወት ያልፋል።

የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተው ቲቢ በአመት 10 ሚሊዮን የሚገመት የአለምን ህዝብ እንደሚያጠቃ ተጠቁሟል።
ከዚህ ውስጥም በአመት 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ የቲቢ ህሙማን ህይወት ያለ፤ፋል ነው የተባለው።
በአብዛኛው በቲቢ በሽታ ከሚጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ከ15 እስከ 54 ዓመት የሚሆነው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚሆኑት መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *