የቀድሞ የጋምቢያ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ክስ ሊመሰረትባቸው ነው።

የጋምቢያ መንግስት ‘በእውነት እና እርቅ ኮሚሽን’ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ በስልጣን ላይ ከቆዩበት ጊዜ ጀምሮ በግድያ እና በሌሎች የተጠረጠሩ ወንጀሎች እንዲከሰሱ የቀረበውን ሀሳብ ተቀብሏል።

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ እንደገለፁት ባለፈው አመት በእውነት እና እርቅ ኮሚሽን (TRRC) ሪፖርት ላይ የተቀመጡትን ከ1994 እስከ 2017 የተገኙ የመብት ጥሰት ጉዳዮችን ልዩ አቃቤ ህግ ይመለከተዋል ብለዋል።
“በእርግጠኝነት መናገር የምችለው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃሜህ ፍትህ እንደሚጠብቃቸው ነው” ሲሉም አክለዋል።

ገለልተኛው ኮሚሽን ጃሜህ እና ተባባሪዎቻቻዉ ግድያ እና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ በጋዜጠኞች፣ በቀድሞ ወታደሮች፣ በፖለቲካ ተቃዋሚዎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለተፈጸሙ 44 ልዩ ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ብሏል።
ጃሜህ እ.ኤ.አ. በ2016 በፕሬዚዳንት አዳማ ባሮው በምርጫ ተሸንፈው ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ሸሽተው ሄደዋል።

“ፍትሕን ወይም የተወሰደውን ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ ከብዙ ዓመታት መጠባበቅ በኋላ ለTRRC እና መንግሥት ምስጋና ይግባውና ዛሬ እውን ሆኖ በማየታችን እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ” ሲሉ ታዋቂው ጠበቃ አሚ ሲላ ተናግረዋል ።
የተጎጂ ቤተሰቦች ግን ወደዚህ ክስ ሂደት የተደረሰበት መንገድ አዝጋሚ እንደነበር ቅሬታ አቅርበዋል።

ጃሜህ ለፍርድ እንዲቀርቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ ጃሜህን አሳልፋ ለመስጠት መስማማት ይኖርባታል።
ሁለት ሶስተኛው የጋምቢያ ፓርላማም ክሱን ማጽደቅ ይኖርበታል መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *