“ባንኮች 1.8 ቢሊየን ብር ተመዝበረዋል” ተባለ፡፡

በባንኮች ላይ በሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተነሳ 1.8 ቢሊየን ብር የሚደርስ ምዝበራ በባለፉት አራት አመታት ማጋጠሙን የፍትህ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓም በሸራተን አዲስ ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት፣ ከደረሰው ምዝበራ ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ ምዝበራው የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነዉ መባሉን ሪፖርተር ጽፏል።

በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው

  • አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣
    *ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና
  • ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተለያየ መልክ የሚከተሉ በመሆናቸው የሚያደርሱት ቀውስና አደጋ ከፍተኛ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *