የድምጽ ብክለትን ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከመጠን በላይ የድምጽ ብክለት ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ከዚህ በፊት በመዲናዋ የድምጽ ብክለት የሚከለክል ህግ ቢኖርም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ ነው የተነገረው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እንደተናገሩት፣ ከተማዋ በድምጽ የብጥብጥ እና የረብሻ ከተማ ከሆነች ሰነባብታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በየመንገዱ በህገ-ወጥ መንገድ ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም፣ የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰዎች የዜጎችን እና የከተማዋን ሰላም እየነሱ እንደሚገኙም ነው አቶ ጥራቱ በየነ የተናገሩት፡፡

አዲስ አበባ ለዜጎቿ እና ለእንግዶቿ የተመቸች ከተማ እንድትሆን፣ የሁሉንም እርብርብ ይጠይቃል ያሉት አቶ ጥራቱ፣ ሁሉንም ከህግ ጋር ማስኬድ ያስፍልጋል ብለዋል፡፡

በዓለማችን ካሉ ከተሞች አዲስ አበባ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት ከሚያስተናግዱ ከተሞች መካከል ከቀዳሚዎቹ ዉስጥ እንደምትጠቀስ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ እና ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የድምጽ ብክልት የሚከለክል ህግ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *