ግብፅ የቀድሞ ፕሬዝዳንታዊ እጩን በ15 ዓመት አስራት ቀጣች::

የግብፅ የወንጀለኛ መቅጫ ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንታዊ እጩን ከከባድ የጉልበት ሥራ ጋር የ15 ዓመት እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡

የ70 አመቱ እና በጠና የጤና እጦት የሚሰቃዩት አብደል ሞኒም አቡል ፎቱህ የሙስሊም ወንድማማችነት ቡድን ጊዜያዊ መሪ ማህሙድ ኢዛት ጋር የሀሰት ዜና በማሰራጨት እና አሸባሪ ቡድንን በመቀላቀላቸው ተከሰው እንደነበር ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በዘገባው መሰረት ሁለቱም ከባድ ክሶች ናቸው።
አቡል ፎቱህ በፈረንጆቹ 2018 ከብሪታንያ ሲመለሱ ነበር ተይዘው ዘብጥያ የወረዱት፡፡
በለንደን በነበሩበት ወቅት የፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲን አገዛዝ በመተቸት በርካታ የሚዲያ ቃለመጠይቆችን ሰጥተዋል።

ተከሳሾቹ በቅጣት ወሳኔ ላይ ይግባኝ ማለት ይችላሉ ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *