ፖግባ ከዩናይትድ ይለቃል

ፖል ፖግባ በዚህ ወር መጨረሻ ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ከክለቡ እንደሚለያይ ማንቸስተር ዩናይትድ ማረጋገጫ ሰጠ ፡፡

የ29 ዓመቱ ፖግባ በ2016 ጁቬንቱስን ለቅቆ ማንቸስተር ዩናይትድን ዳግም ሲቀላቀል በወቅቱ የተጫዋቾች ዝውውር ሪከርድ የነበረ 89 ሚ.ፓ ተከፍሎበታል ፡፡

ዘንድሮ በዩናይትድ ባሳለፈው የመጨረሻ የውድድር ዘመኑ በጉዳት ምክንያት በበርካታ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ሳይችል ቀርቷል ፡፡ 27 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሰልፏል ፡፡

ክለቡ ባወጣው መግለጫ ‹‹ በርካታ ውብ ጎሎችን አስቆጥሯል ፤ ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል ፡፡ በመጨረሻ ግን የዩናይትድ ቆይታው ሊጠናቀቅ ግድ ብሏል ›› ብሏል ፡፡

ፖግባ ለ ሃቭረን ለቅቆ ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው በ2009 ገና የ16 ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር ፡፡

ፈረንሳዊው በሁለት የተለያዩ አጋጣሚዎች በኦልድ ትራፎርድ ባሳለፈው ጊዜ በድምሩ 233 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፏል ፡፡ 39 ጎሎችን አስቆጥሯል ፡፡

አቤል ጀቤሳ

ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.