ሩዲገር የማድሪድ ዝውውሩን ፈጸመ::

አንቶኒዮ ሩዲገር ቼልሲን ለቅቆ በነጻ ዝውውር ለሪያል ማድሪድ የአራት ዓመት ኮንትራት ተፈራርሟል ፡፡

ጀርመናዊው የስፔን እና የአውሮፓ ሻምፒየኖቹን የተቀላቀለው ቼልሲ ያደረገውን የኮንትራት ማራዘሚያ ጥረት ወደ ጎን ብሎ ነው ፡፡
ሩዲገር በ2017 ሮማን ለቅቆ ቼልሲን የተቀላቀለው በ29 ሚ.ፓ ቅድመ ክፍያ መሆኑ ይታወሳል ፡፡

በሰማያዊዎቹ ማሊያ 203 ጨዋታዎችን አከናውኖ 12 ጎሎችን አስቆጥሯል ፡፡ የኤፍ ኤ ካፕ ፣ ቻምፒየንስ ሊግ ፣ ዩሮፓ ሊግ ፣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ እና የክለቦች የዓለም ዋንጫን አሸንፏል ፡፡

ቼልሲ ሩዲገርን ‹‹ ክለቡን በቅርብ ጊዜ ከወከሉ የትልቅ ስብዕና ባለቤቶች አንዱ ›› በማለት ገልጾታል ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.