ከ140ሺህ በላይ ተማሪዎችን መድረስ የሚችሉ የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት ስራ መጀመራቸዉ ተነገረ ።

45 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ “ብሪጂንግ ዘ ዲጂታል ዲቫይድ፣ ኢምፓወሪንግ አወር ስቱደንትስ ዊዝ ዲጂታል ኢጁኬሽን ” በሚል ኢትዮ ቴሌኮም በ66 የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዲጂታል መማሪያ ማዕከላትን ገንብቶ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በአዲስ አበባ እና በክልል ባሉ 66 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ140ሺህ በላይ ተማሪዎችን መድረስ የሚችሉ የዲጂታል ማዕከላትን ገንብቶ በዛሬው ዕለት ማስመረቁን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

“ተማሪዎች ከሌላ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር መረጃ በቀላሉ መለዋወጥ እንዲችሉ ፣ የምርምር ስራዎችን ለማከናወን እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ እና የተሻለ ለማድረግ አስተዋጽኦ ይኖረዋል “ሲሉም ተናግረዋል።

ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት 21 ብሮድባንድ ኮምፒውተሮች መከፋፈላቸውን እና በአጠቃላይ 1 ሽህ 386 ኮምፒውተሮች ለትምህርት ቤቶቹ መከፋፈላቸውንም ገልጸዋል ።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከአዲስ አበባ እና ከክልል ከትምህርት ቢሮዎች በተገኘ መረጃ መሠረት መመረጣቸውን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ በአዲስ አበባ የነበሩ ትምህርት ቤቶችን ማደሳቸውን እና በክልል የሚገኙትን ግን እንደ አዲስ ገንብተው ስራ ማስጀመራቸውን ተናግረዋል ።

ከ66ቱ ትምህርት ቤቶች 18ቱ በአዲስአበባ ቀሪዎቹ 48 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።

በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *