ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶች ሰጥተዋል።
በዚሁ መሰረት፥
- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር
- አቶ ካሊድ አብዱራህማን – በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል
- አቶ ወንድሙ ሴታ – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
- አቶ ሄኖስ ወርቁ – የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ሸመቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፦
- ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ – የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
- አቶ አበራ ታደሰ – የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሹመዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም











