የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የ2014 አፈጻጸም እየተገመገመ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመሩት በዚህ መድረክ ላይም የእያንዳንዱ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ያለፉት 10 ወራት አፈጻጸም ቀርቧል።

የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የፕላን እና ልማት ሚንስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፣ በዓመቱ ሀገሪቱ በውጫዊ እና ውስጣዊ ጫናዎች ውስጥ ብታልፍም፣ ኢኮኖሚውን እንቅስቃሴው ሳይስተጓጎል ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል።

ለዚህም የበጋ ስንዴ፣ የሸቀጦች ወጭ ንግድ፣ ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨትን ጨምሮ በዓመቱ የተከናወኑ ስራዎች ትልቅ ፋይዳ እንደነበራቸው ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.