የሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ ሰኔ 2 /2014 ይጀመራል ተብሏል፡፡

በዘመቻ መልክ የኮቪድ ክትባት ሲሰጥ ይህ ሶስተኛው ምዕራፍ ሲሆን፣ ዘመቻው ሰኔ 2 /2014 ይጀመራል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት ዘላለም ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ክትባቱን ያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች 24.5 ሚሊዮን ደርሷልም ነው የተባለው።

በዚህ በሶስተኛው ዙር ዘመቻም 25 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ክትባት ያገኛሉ ተብሎ መታቀዱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ይህ ክትባት ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር ከ12 አመት በላይ ለሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ይሆናል ነው የተባለው።

በኢትዮጲያ መጋቢት 4/ 2014 የኮሮና ቫይረስ መግባቱ ከታወቀበት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 475 ሺህ 12 ሰዎች በላይ በቫይረሱ መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ከ7 ሺህ 515 በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን ነው ዶ/ር መሰረት የገለፁት።

ዶ/ር መሰረት ክትባቱ በታቀደው መሰረት ተግባራዊ እንዲደረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉበት ገልፀው፣ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2022 (በተያዘው አመት መጨረሻ ) ከአጠቃላይ ህዝቧ 40 በመቶ የሚሆነውን ክትባት የማዳረስ እቅድ መያዟን ጠቁመዋል።

በረድኤት ገበየሁ

ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *