የእሳት አዳጋን በስልካቸዉ ሲቀርጹ የነበሩ ሰዎች በአደጋዉ ህይወታቸዉ አለፈ፡፡

በደቡባዊ ባንግላዲሽ በሚገኘው የመርከብ ኮንቴይነሮች ማከማቻ መጋዘን ላይ ለተነሳው የእሳት ቃጠሎ ምላሽ ለመስጠት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታዉ ተገኝተዉ አደጋዉን ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ላይ ነበሩ፡፡

የሚቃጠሉ ኮንቴነሮች ውስጥ ኬሚካል መኖሩን ግን ማንም ከግምት ዉስጥ ያስገባ አልነበረም፡፡
በዚህም የፍንዳታ አደጋ ሲከሰት የእሳት አደጋ ተከላካይ ባለሙያዎችን ጨምሮ ቢያንስ 41 ሰዎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

እንደ ኒዮርክ ታይምስ ዘገባ በፍንዳታው ከሞቱት መካከል እሳቱን በስልካቸው ለመቅረጽ ወደ ቦታው የቀረቡ ነዋሪዎች እንደሚገኙበት አመልክቷል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *