75 ዓመታትን ያስቆጠረዉ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት፡-

የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት 75ኛ አመት የምስረታ በአሉን ከሰኔ 21-23 2014 ዓ.ም እንደሚያከብር አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሠንበት ሸንቁጤ 75ኛ አመት የምስረታ በአሉን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር ከሰኔ 21-23 2014 የሚቆይ እና ምስረታውን የሚያስታውሱ የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአዋጅ ከተቋቋመበት 1939 ዓ.ም ጀምሮ በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፉን ያስታወሱት ወ/ሮ መሰንበት፣ ከእነዚሁ መካከል ለምክርቤቱ ዛሬ ላይ መድረስ አስቷፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና መርሃግብር እንደሚኖር አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የምክር ቤቱን የ75 አመታት ጉዞውን የሚያስረዳ ዶክመንተሪ፣ የመፅሃፍ ዝግጅት፣ የፎቶ አውደ ርእይ እና የውይይት መድረኮችንም እንደሚያዘጋጁ ሰምተናል፡፡

በቀጣይ የአዲስ ቻምበር ዘመኑን የሚመጥን የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን በማቅረብ፣ የግሉን ዘርፍ እና መንግስት የሚያስተሳስር ሆኖ በመቀጠል ለሃገራችን የመፍትሔ አካል እንደሚሆም ወ/ሮ መሰንበት ተናግረዋል።

በአብዱሰላም አንሳር

ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *