መረጃዎችን በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እያደራጀሁ እገኛለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአገልግሎት አሰጣጡንና የአሰራር ስርዓቱን ለማቀላጠፍ፣ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ተግባራዊ በማድግ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተገልጋዬችን መረጃ ዲጂታላይዝ ለማድረግ ሰራውት ያለውን መረጃ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ አስር ወራት 5 ሺህ 158 ተቋራጮች፣ አማካሪዎችና ባለሙያዎች፣300 ሺህ 48 የግንባታ ፈቃድ፣100 ሺህ 62 የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር መረጃዎች እንዲሁም 2 ሺህ 369 መረጃዎች ከ2010 ዓ.ም በፊት የተፈቀዱ የግንባታ ነክ መረጃዎችን በሃርድና በሶፍት ኮፒ የማደራጀት ስራ መስራቱን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍኤም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 2 ሺህ 158 መረጃዎች ስካን በማድረግ ማደራጀት መቻሉን ያስታወቀው ባለስልጣኑ በቀጣይ የዲጂታል የመረጃ አያያዝ ስርአትን በማዘመን አግልግሎቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *