ስራቸውን በአግባቡ በማይወጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮችና አምራቾች ላይ እርምጃ እወስዳለው ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡

የሚኒስቴር መ/ቤቱ የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሃመድ ከ230 በላይ የሲሚንቶ አምራቾችና አከፋፋዮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሲሚንቶ ጉዳይ ሃገራዊ ችግር እንደሆነና ለዚህም ችግር መከሰት የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትን ተከትሎ የግብይት ስርዓት ላይ የሚስተዋለው ውስብስብ ችግር የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

መንግስት የሲሚንቶ ምርት ዋጋ ላይ የቁጥጥር ስርዓቱን ማንሳቱን ተከትሎ በፊት ሲሸጥ ከነበረበት ዋጋ ከእጥፍ በላይ ጭማሪ በማድረግ፣ በአሁኑ ወቅት ሲሚንቶ በገበያ ላይ እስከ 1200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ሚንስትር ዴኤታዉ ገልጸዋል፡፡

ይህም ያልተገባ ድርጊት መንግስት ካሁን ቀደም በሲሚንቶ የግብይት ሂደት ውስጥ ያስቀረውን የዋጋ ቁጥጥር ስርዓት በድጋሜ እጁን እንዲያስገባ እያስገደደው እንደሚገኝና በነዚህ ህገ ወጥ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ መናገራቸዉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *