በአዲስ አበባ ክረምቱን ተከትሎ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ 141 ቦታዎች ተለይተዋል ተባለ፡፡

ክረምቱን ተከትሎ በመዲናዋ የጎርፍ አደጋ ይከሰትባቸዋል በተባሉት ቦታዎች የኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በአዲስ አባባ በተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ የሚከሰትባቸው ቦታዎች ተለይተው የጥንቃቄ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በከተማዋ ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከተለዩት አካባቢዎች መካከል አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አንደኛው ሲሆን ኮልፌ ቀራኒዮም ከፍተኛ ተጋላጭ ተብለው ከተለዪ ቦታዎች ይገኝበታል፡፡

እንዲሁም ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ አራዳ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ደግሞ በከፊል ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብሏል፡፡

ህብረተሰቡ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሚያደርጉ የፈሳሽ ማጋጃች ቱቦዎች ባግባቡ እንዲጠቀምባቸው ባለሙያው መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡
ባሳለፍነው 2013 ዓ.ም 11 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል፡፡

በሔኖክ ወ/ ገብርኤል

ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *