የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርተፍኬት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ቦርዱ 6ተኛውን ብሄራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እና መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማካሄዱ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫው ለተሣተፉ የዞን አስተባባሪዎች፣ ምክትል የዞን አስተባባሪዎች፣ የምርጫ ክልል ኃላፊዎች፣ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ እንዲሁም ዳታ ኢንኮደሮችና የአይ.ሲ.ቲ ባለሞያዎች ሰርተፊኬት መስጠት መጀመሩን ነው ያስታወቀው፡፡

በምርጫ ሂደቱ የተሳተፉ ባለሙያዎችን ያመሰገነው ቦርዱ በምርጫው ላይ የነበራቸውን ተሣትፎ የሚያረጋግጠውን የምስክር ወረቀት በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ፖርታሉን ይፋ አድርጓል፡፡

የምስክር ወረቀቱ የሚመለከታቸው ሠራተኞችም የምስክር ወረቀት ፖርታሉ ላይ የሚጠየቁትን መረጃዎች በማስገባት የምስክር ወረቀታቸውን መውስድ ይችላሉ ያለው ቦርዱ http://nebecertificate.org.et ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም እና የባንክ ሂሳብ ቁጥርን በማስገባት የምስክር ወረቀቱ ላይ ያሉ መረጃዎች ትክክለኛ መሆናቸውን አረጋግጦ ማግኘት እንደሚቻልም አስታውቋል::

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *