የዓለም ባንክ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ውድቀት ስጋት እንዳለ አስጠንቅቋል::

በኮቪድ ወረርሽኙኝ የተዳከመዉ ኢኮኖሚ በዩክሬን እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት ሲጨመርበት የአለም ሀገራት የኢኮኖሚ ውድቀት እያጋጠማቸው መሆኑን የአለም ባንክ አስጠንቅቋል።

በአውሮፓ እና በምስራቅ እስያ ያሉ ያላደጉ ሀገራት ትልቅ የኢኮኖሚ ውድቀት ይጋጥማቸዋል ብሏል።

ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ዝቅተኛ ዕድገት – “stagflation” ተብሎ የሚጠራው – ደግሞ ከፍተኛ ነው ሲሉ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ተናግረዋል፡፡

የምግብ እና የኢነርጂ ዋጋዎች መጨመር የኑሮ ውድነቱን እንዲያባብሰው እንዳደረገው የሚገለፁት ሃላፊው፣ ይህ ችግር እየተስተዋለ የሚገኘው በድሃ አገሮች ብቻ እንዳልሆነም አብራርተዋል።

አንድ ጥናት እንደሚያሳየው ከስድስት የብሪታንያ ቤተሰቦች አንዱ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል፡፡

ይህን ተከትሎ የአለም ባንክ ከዕዳ ስረዛ ጀምሮ ሀገራት በምግብ ኤክስፖርት ላይ ገደብ እንዳይጥሉ አሳስቧል።

እንደ የዓለም ባንክ ትንበያ እ.ኤ.አ. በ 2022 በከፍተኛ ሁኔታ ኢኮኖሚያቸው ከሚቀንሱ የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬን እና ሩሲያ ተቀምጠዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ 2021 እና 2024 ባሉት ዓመታት ዓለም አቀፍ እድገት በ 2.7 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህም በ 1976 እና 1979 መካከል ከታየው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ከእጥፍ በላይ ብልጫ ያለው ሲሆን ፣ዓለማችን የመጨረሻ ደረጃ የዋጋ ንረት እንዳጋጠማት ነው ትንበያው የጠቆመው፡፡

እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ መጨረሻ ላይ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የሚያስፈልገው የወለድ ምጣኔ በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ፣ እ.ኤ.አ. በ1982 ዓ.ም የነበረውን ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ድቀት እና በታዳጊ ገበያ እና በማደግ ላይ ባሉ ኢኮኖሚዎች ላይ ተከታታይ የሆነ የፋይናንስ ቀውሶችን ነክቷል ሲል ሪፖርቱ ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ጽፏል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.