ዩክሬን ወደቦቿን ከፈንጂ ካፀዳች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እንደምታደርግ ሩሲያ ገለጸች፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ይህንን ያስታወቁት በቱርክ በነበራቸው ቆይታ ሲሆን ዩክሬን የገዛ ወደቦቿን በፈንጅ አጥራለች ብለዋል፡፡
ሃገሪቱ ጥቁር ባህር ወደቦቿን ከፈንጅ ካፀዳች የእህል ምርቶች ያለምንም ስጋት ሃገራቸዉ እህል እንዲጫኑ እንደምታደርግ አስታዉቀዋል፡፡

ይህ ፕሬዝዳንቱ ቭላድሚየር ፑቲንም ያረጋገጡት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ሩስያ በአለም የምግብ ቀውስ መባባስ ምክንያቶች ውስጥ ድርሻ የላትም ብለዋል፡፡
ጦርነቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፣ የሩስያ ሃይሎች በምስራቅ ዩክሬን የምትገኘውን ስትራቴጂያዊ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በሴቨሮ-ዶኔትስክ ከተማ የሚገኙ የዩክሬን ሃይሎች አፈግፍገው ሁነኛ ቦታ እንዲይዙ መመከሩን በኬቭ የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች መናገራቸውም ተዘግቧል፡፡

በማሪዮፖል እጃቸውን የሰጡ ከ1000 በላይ የሚሆኑት የዩክሬን ሰራዊት አባላት ለምርመራ ወደ ሩስያ መጓጓዛቸውንም የሩስያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.