የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2014 በዋለው ችሎት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ አዟል።
በትላንትናው ዕለት በዋለው ችሎት ላይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራ መጨረሱን ገልፆ መዝገቡን ለክልሉ አቃቤ ህግ ሊልክ መሆኑን አስታውቆ የነበረ ሲሆን፤ የክልሉ አቃቤ ህግም ምርመራው በማለቁ የክስ መመስረቻ የ15 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።
የተከሳሽ ጠበቃም ምርመራው ካለቀ ዋስትና የሚያስከለክል ክስ ባለመኖሩ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ዋስትና የሚከለክል ሆኖ ስላላገኘው በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ አዟል ሲል የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታዉቋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም











