የበርበራ ወደብን በተመለከተ መረጃ እያጣራሁ ነዉ….መንግስት

ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን እንዳጣች የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡

የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ የሚወጡ መረጃዎች የኢትዮጵያ መንግስት ማሟላት የነበረበትን የባለቤትነት መስፈርቶች በጊዜው ባለሟሟላቱ ባለቤትነቱን መነጠቁን ያትታሉ፡፡

ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች ሲልም ያክላል፡፡

ሳምንታዊ መግለጫ እየሰጡ የሚገኙት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ደግሞ የበርበራ ወደብን በተመለከተ መንግስት መረጃን እያጣራ ይገኛል፡፡

የሱዳን ወረራ ጉዳይ በተመለከተ ባነሱት ሃሳብ ደግሞ ኢትዮጵያ አሁንም የተሸለዉ መፍትሄ በመነጋገር ችግሮችን መፍታት ይገባል ብላ ስለምታምን ሱዳን ከድርጊቷ ትቆጠባለች የሚል ተስፋ አለን ብለዋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *