የጎርፍ አደጋ ሰለባ ሆነዉን ህጻን አሁንም እያፈላለገ እንደሚገኝ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ በየላዛሪስት ካቶሊክ ትምህርት ቤት ከትላንት ወዲያ በጎርፍ የተወሰደው ህጻን ልጅ አለመገኝቱን ተናግሯል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ ባሳለፍነው ዕረቡ እለት ቀን ዘጠኝ ሰአት አካባቢ በጣለው ዝናብ ምክንያት አንድ የስድስት አመት ህጻን ልጅ በጎርፍ መወሰዱ ይታወሳል፡፡

በጎርፍ የተወሰደው ህጻን ልጅ ከትምህርት ቤት መልስ ወደ ቤቱ በመሄድ ሳለ ነው በጎርፉ የተወሰደው ተብሏል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በጎርፍ የተወሰደው ህጻን ልጅ አስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መርማሪዎች በአነፍናፊ ውሻ በመታገዝ ፍለጋውን እያካሄዱ ይገኛሉ ብለውናል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በዚህ ፍለጋ ወቅት ሌሎች አስከሬኖች እንደተገኙ የሚዘዋወረዉ መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲልም ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ወደ ቤት ሲያሰናብቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አቶ ንጋቱ ማሞ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *