መስከረም አበራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ::

“ኢትዮ ንቃት” የተሰኘ የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መስከረም አበራ፤ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ትዕዛዙን ዛሬ ሰኞ ሰኔ 6፤ 2014 ያስተላለፈው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በነበረው የችሎት ውሎ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተጠርጣሪዋ ላይ እያከናወነው ያለውን ምርመራ አጠናቅቆ እንዲያቀርብ ተጨማሪ ስድስት ቀናት ፈቅዶ ነበር።

ፖሊስ በዛሬው ችሎት ምርመራውን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 14 ቀናትን ጠይቋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፤ በመስከረም አበራ ጠበቆች በኩል የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ መቀበሉን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

መስከረም አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው ከ23 ቀን በፊት ግንቦት 13፤ 2014 እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *