አማራ ባንክ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ ይጀምራል፡፡

በምስረታ ላይ የቆየው የአማራ ባንክ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ባንኩ በዛሬዉ እለት አስታውቋል።

የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ ባንኩ ሰኔ 11 በ70 ቅርንጫፎች ስራውን በይፋ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

እስከ ሰኔ ሰላሳ ድረስም ሰራ የሚጀምሩ ቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል።

ሰኔ 11 ስራውን በይፋ የሚጀምረው ባንኩ በእለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ ይከፍላል ተብሏል።

በእለቱ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም የእንኳን ደስ ያላችሁ ስጦታም ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 06 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *