በማይሆን መንገድ መከላከያን የነካ ይጠየቃል፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፡፡

እያንዳንዱ ሰው መብቱን ብቻ ሳይሆን ግዴታውን በሚገባ ማወቅ አለበት ብለዋል፡፡
ከመከላከያና ከጋዜጠኞች እስር ጋር ተያይዞ ለተወካዮች ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ከአሁን በኋላ መከላከያን በማይሆን መንገድ የነካ ይቀፈደዳል ምክንያቱም መከላከያ ከሌለ እኛ የለንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደፈለጉ የመከላከያን ክብር እየነኩና እያጠለሹ አልታሰርም ማለትም አይሰራም ብለዋል ዶ/ ዐብይ ፡፡

ስድብና ጥላቸው በመካለከያ ብቻ ሳይሆን በመሪነት ደረጃ ቢሆን እንደኔ የተሰደበ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ባልተገባ መልኩ መከላከያንም ሆነ እኔን መስደብ ተገቢ አይደለም ደግሞም ያስጠይቃል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሰዳቢው ስድብ ሲያስከትል መብቱ የሚሆንበት ፤ተሰዳቢው ለመጠየቅ ደግሞ ሲፈልግ ትክክል አይደለም የሚባልበት መንገድ የለምና እየሆነ ያለው ነገር ጥሩ አይደለም ሲሉ በተወካዮች ፊት ተናግረዋል፡፡

ጋዜጠኞችን በተመለከተ ማፈን ተረት ተረት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህን ያደረገ ተቋም እንደሌለና አለ ከተባለ ግን እንደማንኛውም ወንጀለኛ እንደሚጠየቅ ተናግረዋል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *