‹‹የስኳር ፍብሪካዎች እስከ 2010 የነበረባቸዉን ዉዝፍ ሂሳብ አሁን ነዉ የዘጋነዉ፡፡›› ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀርበዉ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸዉ፡፡

በዚህም ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ከስኳር ጋር የተያያዘ ጥያቄ ቀድሞ የነበሩትን 4 የስኳር ፋብሪካዎች ላይ ጭማሪ አድርገን ወደ 9 አሳድገናል፣ከዚህ በፊት ከነበረዉ አገዳ የማምረት አቅምም ከ30 ሺህ ወደ 100ሺህ ሄክታር አሳድገናል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ 200 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም ወደ 360 ሺህ ቶን የማምረት አቅም ላይ ደርሰናል ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ይህን ሁሉ ማምረት እየቻልን ታዲያ ዋጋ ለምን ይጨምራል የሚለዉ ጥያቄ ተገቢ በመሆኑ ይህንንም ለማስተካከል እንሰራለን ብለዋል፡፡

በተገባዉ ቃል መሰረት እየሰራን እንገኛለን ስለሆነም ስራችን ሊናቅ አይገባዉም ሲሉ ለተወካዮች ምክርቤት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ማሻሻያዎች እንዳሉ እናምናለን ነገር ግን በቂ አለመሆኑንም እናዉቃለን ስለዚህ ያለዉን የፍላጎት ዕድገት እና የምርት ዕጥረት ለማስተካከል እንሰራለን ብለዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *