25 በመቶ የሚሆነው የእርሻ መሬት በትራክተር ማረስ ተችሏል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፡፡

በዚህ አመት 25 በመቶ የሚሆነው ሃገራችን የእርሻ መሬት በትራክተር ማረስ መቻሉን ጠቅላይ ሚነስተር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
በሃገራችን ግብርና ባልተለመደ መልኩ በበሬ ይታረሱ የነበሩ የእርሻ መሬቶች ፤ ዛሬ ላይ 5 ሺ በሚሆኑ ትራክተሮች ታርሰው በመህር ምርት 336 ሚሊየን ኩንታል ማምረት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልጸዋል፡፡

በሚቀጥሉት አመታት ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ ትራክተሮችን ቀጥር 10 ሺ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሃገራችን ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት ይህ ውጤት ሊያስመሰግን እንጂ ሊያስወቅስ አይገባም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለግል ሴክሮች በብድር ከተሰጡ በጀቶች መካከል 43 በመቶ ለግብርና ስራዎች በብድር መልክ የተሰጠ ሲሆን ይህም አጠቃላይ ለብድር ከተዘጋጀው በጀት አንድ ሶስተኛውን እንደሚሸፍን ጠቁመዋል፡፡

ያለፈውን አመት ሳያካትት በዚህም አመት ብቻ ለግብርና ስራዎች 15 ቢሊየን ብር ድጎማ ተደርጓል ያሉት ዶክተር አብይ ይህም ከ1 ሺ ቶን በላይ ምርጥ ዘር ለዘርፉ ድጎማ መደረጉ የሳያል ተብሏል፡፡

በመጨረሻም ኢትዮጵያ ከአግዋ ታግዳ ባለችበት በዚህ ወቅት፤ በዘርፉ ከፍተኛ ትርፍ ማግኘት መቻሉን ተናግረወል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሰኔ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *