በዓለም በዓመት 700ሺህ ሰዎች ፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶችን በተላመዱ በሽታዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ።

ፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶችን በተላመዱ በሽታዎች ምክንያት በቀን ከ2ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።

ይህ የተባለው አስረኛ አመት የፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶች-የበሽታ አምጪ ጀርሞች መላመድ ቀን እየተከበረ ባለበት ጊዜ ነው።

የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ሰይፉ ፀረ ተህዋስያን መድሀኒቶችን በተላመዱ በሽታዎች አማካኝነት እኛ እያወራን ባለንበት በዚህ ሰአት ወደ 1ሺህ ሰው ህይወቱን ያጣል ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በዚህ ከቀጠለ እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት በ2050 በየአመቱ 10 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡም አክለው ገልጸዋል።

የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒት መላመድ ችግር እንደ መንስኤ ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል የቁጥጥር ስርአት ማነስ፣የኢኮኖሚ ችግር ፣የእውቀት ማነስ እንዲሁም መድሀኒት መዋዋስ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ስዩም ወልዴ ገልጸዋል።

መድሀኒቶችን አለአግባብ በመጠቀም ከሚከሰቱ በሽታዎች መካከል ከ60-80 በመቶ የሚሆኑት ተላላፊ በሽታዎች መሆናቸው ተነስቷል።

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 08 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *