የሶስቱ አውሮፓ ሃገራት መሪዎች ኬቭ እንደሚገኙ ተሰምቷል፡፡

በቀጠለው የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገደች ለምትገኘው ዩክሬን አጋርነታቸውን ለማሳየት ወደ መዲናይቱ ማቅናታቸው ተነግሯል፡፡

መሪዎቹ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ እንዲሁም የጣሊያኑ ማሪዮ ድራጊ ናቸው፡፡

መሪዎቹ በጋራ ከሚመክሩባት ጠበብ ካለች ክፍል የተነሱት ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጨ ሲሆን የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ከሰአታት በሁዋላ አጊኝተው ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የሃገራቱ ‹‹አለንልሽ›› ከቃል ያለፈ ላለችበት ውጥንቅጥ ቅንጣት ያልፈየዳት ዩክሬን ዛሬም ጦርነቱ እንደቀጠለባት እና በየእለቱ የምታጣቸው ወታደሮቿንም መታደግ አልቻለችም፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ሰኔ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *